Posts

Showing posts from September, 2026

ስንት እንደ ነበሩ

Image
        የፀደይ ወቅት እንቅልፍ በፀደይ ተኝቼ ሳላውቀው ጎህ ቀዶ ጭልጥ አርጎ ወስዶኝ እንቅልፌ አልጋ ወዶ ወፎች ሲዘምሩ በየመስኩ ማዶ ሰማሁና ነቃሁ ቀኑ ሞቆ ማልዶ ለካስ በዚያ ሌሊት ዶፍ ያዘለ ዝናም ካውሎ ነፋስ ጋራ ዘንቦ ኖሮ በጣም ሌሊት የወረደው የዝናብ ማዕበል መብረቅ ወይ ነጎድጓድ ይህ ነው የማይባል ስንቱን ጽጌያት ነው የፀደይ ቀዘባ ጠራርጎ ያጨደው ያረደው አበባ መርገፋቸው እንጂ እንዲያው በድምሩ ቊጥራቸውን ማን ያውቃል ስንት እንደ ነበሩ ~ ገሞራው (ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ) ለንደን (በአውሮጳ 1979)

ሕይወት ምሥጢር

Image
የሕይወት ምሥጢር ቋጠሮ አረንጉዋዴ ቸብቸቦ ውስጥ የጽጌረዳ እምቡጥ የወዳፍዋን ቋጠሮ ሙጥሙጥ በትንሹ ብቅ አድርጋ ስታጒዋጒዋ ስታጒዋጒዋ ድብቅ ውበት። እናይ ይሆን ፈንድታ ስትቀይጥ ተቅላልታ ቀለሙን አረንጉዋዴነቱን። ፍንዱ ተስጣቶላት የውስጥ ሀብት ዑደትዋ፣ ቅላትዋ ተደራርቦውም እንጂ የቀያይ ጆሮችዋ። ማርያም ማርያም የምለው ለውበት ልደት ነው፦ ለጽጌረዳዎች ውበት፤ ለሰው ልጆች ውበት፤ ለሕይወት ውበት ድብቅ፤ የፍልቅቅ ፍልቅቅ እንደጽጌረዳዋ ፈንድቶት ተስጣቶት እንዲያፍካካን ሕይወታችንን ለውጦት። ~ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው“የተስፋ እግር ብረት” ገጽ 10-11 መስከረም 1969 ዓ.ም.፣ ብ/ሰ/ማ/ቤት፣ አ.አ. ግጥሙ ለመጀመሪያ ጊዜ 19 June 2014 ኢትዮፕያንቸርች ላይ ታተመ።

አዲስ መንግሥት

አዋጅ! አዋጅ! " አካታች የሽግግር መንግሥት " ሊቋቋምልን ነው! እልል እንበል? ከተለያየ ጎሳና ዓላማ ተነሥታችሁ "ሁሉን አካታች" እንዴት ልትሆኑ ትችላላችሁ? የለያያችሁም ያስተባበራችሁም ዐቢይ እንዴት ሊሆን ይችላል? ዐቢይ ሲወገድ ብትንትናችሁ እንደሚወጣ አስተውላችኋል? ወይስ ጊዜው ሲደርስ ልታስቡበት ነው? የየመንደራችሁ ሕዝብ እንዴት ያምናችኋል? ህወሓት ከዚህ የተለየ ምን አደረገ? በአማራ በኦሮሞ በደቡብ ስም ኢሕአዴግ አሰኝቶ አደል ህወሓት አዲሳባ የገባው? ታዲያስ? ትምህርት ቤት ገብታችሁ ከሆነ፣ ምን ዓይነት ትምህርት ቤት እንደ ተማራችሁ አላውቅም። ታሪክ የሚባል አንብባችሁ የምታውቁ አትመስሉም። ደሃው ሕዝብ ለናንተ ሥልጣን መያዝ ለምን ፍዳውን ይቁጠር? ማናችሁም የህወሓትን ወይም የሻብያን ያክል የጦር ድርጅትና ልምድ የላችሁም። ዐቢይ ሲወገድ ያው ከህወሓት/ሻብያ ኪስ ገቢ ናችሁ።

የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር

Image
 

አዲስ

Image
 

መንግሥት ተለዋውጦ ሕዝብ የተረሣበት

አገራችን  ዓይነተኛ መሪዎች የነበሯት ዘመን ነበር። አገር ወዳድ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ። ምን ያደርጋል ታዲያ? ትውልድ ይጠይቅ ለነበረው ጥያቄ ቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻሉም! ዘገዩ። ከ13 ዓመት በፊት እነ ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ ሞክረው ከከሸፈባቸው የመንግሥት ግልበጣ ምንም አልተማሩም። ከ13 ዓመት በኋላ የባሰ መጣባቸው፤ መንግሥቱ ኃይለማርያም የተባለ ሻለቃ። ሲያዋርዳቸው። እስከ ዛሬ የሚያቃጥለኝ፣ አለህግ አለርኅራኄ መገደላቸው ነው።  ከዘውዱ አገዛዝ በኋላ በደርግ ዘመን የተነሡትም የማያሳፍሩ አገር ወዳድ መሪዎች ነበሩ። የቀድሞዎቹ ዘገዩ፤ ያሁኖቹ ተጣደፉ። በጥድፊያ ብዙ አጠፉ። እግዚአብሔርን ናቁ። ያለርኅራኄ ያለፍትኅ ተገዳደሉ።  ዛሬ ያለንበት ውድቀት (ከአዲሳባ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛና ከ3ኛ ድግሪ ምሩቃን ብዙዎቹን በንጉሡም በደርግም ከነበሩት ጋር ማስተያየት ጨርሶ የማይታሰብ ነው። ነገሩ ጠ/ሚ ዐቢይ እንደሚሰብኩን አይደለም። አገርን በባዶ ወረቀት/ያለእውቀት፣ በማዕረግና በወዳደቀ ዩኒቨርሲቲ ማልማት ጨርሶ አይቻልም። ሚንስትሩና አብረዋቸው ያሉት ጧት ማታ እንደ ድግምት ብልጽግና ብልጽግና ይሉናል። አገር ለመምራት የበቁ ዜጎችን ማሠልጠን እስካልተቻለ ግን፣ አገራችን የቱሪስት ገንዘብ ማራገፊያ፣ የቱጃር ዐረቦች መናኻሪያ እንኳ ብትሆን፣ ዜጋ ከጫማ ጠራጊነት ከለማኝነት አይወጣም። እህቶቻችን ባልባሌ ሥፍራ ከመዋል ውጭ ለራሳቸውም ላገራቸውም አይበጁም። በገዛ አገር ባእድ መሆን ነው።  እነ መንግሥቱ የአፄ ኃይለሥላሴን ስህተት ለማረም ተነሡ። የባሰ አበላሽተው ተወገዱ። እነ መለስ ዜናዊ የአፄ ኃይለሥላሴንም የደርግንም ለማቃናት ተነሡ። የባሰ አንጋድደው፣ ራሳቸውም ተወገዱ።  ከእነ መለስ አብራክ የተገኙት ዐቢይ፣ ከ10 ዓመት ንግሥ በኋላ...

Goodness, Peaceful, Godliness, Holiness

Why We Should Pray for Those in Authority  ... the one in authority is  God’s servant for your good.     Romans 13:3-4   ... that we may live  peaceful and quiet lives  in all godliness and holiness.     1 Timothy 2:1-2  

World History

Obama Factor: Ethiopians and Their Place in World History by Mitiku Adisu Important paleontological findings of the past three decades have identified Ethiopia as providing the firmest clue to human origins and to ‘conceptual thinking.’ This statement is, however, too general for our present purposes. With Barack Obama taking center stage and Abraham Lincoln’s 200th birthday approaching we may want to revisit specific contributions Ethiopians have made to world community. In an earlier post we cited that the Luo in Kenya, Southern Sudan and possibly Uganda claim Obama as one of their own; Ethiopians, on the other hand, opted to rename him Brook [blessed v. blessing] in the hope that he will be the one blessing we need to end the deception and misery being carried out in the name of democracy. But unlike Kenyans and Sudanese we already have Abe Lincoln, Alexander Pushkin, and Peter Ustinov in our list of notables. How so? Well, Abe Linco...

ምክክር ምክክር ምክር የማይሰማ ማ ይሆን?

የምክክር ኮሚሽኑ የተጠቃለሉ አጀንዳዎችን በሚቀጥለው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ ተገለጸ። የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ2018 ዓ.ም ዋና ዋና ክንውኖችና ቀጣይ ሥራዎችን አስመልክቶ ጷጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ፣ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርአያ (ፕሮፌሰር) የተጠቃለሉ የአጀንዳ የውሳኔ ሐሳቦች መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ ተናገሩ። ይህም የሚሆነው ለተሳናባቾቹ የፓርላማ አባላት ስንብት ከመደረጉ በፊት መሆኑን ተናግረዋል። 400 አጀንዳዎች እየተደራጁ መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፣ መንግሥት የአጀንዳ ትግበራን የሚከታተልበትን የዕቅድ ስትራቴጂ አስመልክቶ ራሱን የቻለ ምክረ ሐሳብ ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆናቸውን አስረድተዋል። [ሪፖርተር ጋዜጣ በፌስቡክ ገጹ፣ መስከረም 1/2019 ዓም] ኮሚሽኑ ምን ያህል ነፃ እንደ ሆነ ይታያል። የገዥው ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ከሆነም ይታያል። የራሱን ሥራ ሪፖርት መንግሥት ሳንሡር ሳያደርገው በቀጥታ ለሕዝብ ማሠራጨት ይችላል? ያ ካልሆነ ኮሚሽነሩ፣ ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ ሥልጣኔን እለቃለሁ ብለው እንደ ነበር አንርሳ! በሌላ ሥፍራ እንዳመለከትኩት፣ የኢትዮጵያ ችግሯ እርስበርስ አለመተማመን ነው፤ መተማመንን ሳይሆን አለመተማመንን ሥራዬ ብሎ የሚዘራ አመራር መኖሩ ነው!

ሰላም በአዲሱ ዓመት

ለ2019 ዓም ዘመን መለወጫ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የተላለፈ መልእክት ። የሚንስትሩን ቃል አንባቢ ከሕዝቡ ኑሮ ጋር እያስተያየ በጥንቃቄ ያንብብ። በያመቱ ይህን የመሰሉ የምኞት መግለጫዎችን ሰምተናል። ጥያቄው፦ ዐቢይ ሥልጣን ከያዙበት ከ2010 ዓም ጀምሮ የሕዝቡ ኑሮ ምን ያህል ተሻሻለ የሚለው ነው። እርግጥ ነው፣ አገር ማስተዳደር ቀላል አይደለም፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያለች አገር። ዋነኛው ችግር አለመተማመን ነው። ዐቢይን ሕዝብ ያምናቸዋል? ዐቢይ ሕዝብ እንዳያምናቸው ድርሻቸው ምን ያህሉ ነው? አጻጻፋቸው ሁልጊዜ በ"እኛ እና በ"እነርሱ" ከፋፍሎ ነው፦ እነዚያ "ሕዝብ የከፋፈሉና የጨረሱ ..." ተብለዋል። (እኛ ግን) "አስደናቂ ታሪኮችን እየሰራን ነው።" "ፈጣሪ" ከእኛ ጋር ነው... ከእነዚያ ጋር ግን አይደለም! እውነቱ ይህ ነው፦ ብዙሓኑ ሕዝብ ይኸ ዓይነት ንግግር የተጋነነ እንደ ሆነ አውቆ እጅ እጅ ብሎታል። ከመሰልቸቱ ብዛት ልቡን ሰጥቶ አያደምጠውም። ይኸ የሕዝብ አኳኋን ለአገር መሪ ትልቅ አደጋ ቋጥሯል። አፄ ኃይለሥላሴን መንግሥቱ ኃይለማርያምን መለስ ዜናዊ አገር የከዳቸው ድንገት ባንድ ጀምበር አይደለም። ቀድሞውንም ከድቷቸው ኖሮ ጊዜ ሲፈቅድለት የሸሸገውን ልቡን ገልጦ ነው። እግዚአብሔር እግዚአብሔር የሚሉት ዐቢይ፣ ልባቸውን እንዲመክርላቸው ቢፈቅዱለት ለርሳቸውም ለአገርም በበጀ። ሌላኛው ችግር፣ ዐቢይ መስማት የማይፈልጉት እውነታ በአደባባይ እንዳይነገር ማገዳቸው ዋጋ ማስከፈሉ ነው። የተከበቡት ከታሪክ እውነት በራቀ ምኞትና፣ ሊሰሙት በሚሹት ቃላት በሚክቧቸው አድርባዮች ነው። ከላይ የጠቀስዃቸው ሦስት መሪዎችን ከሕዝብ ያራቃቸው ለውርደትና ለውድቀት የዳረጋቸው እንዲህ ዓይነቱ የሕዝብ ስሜ...

መዝሙር እና ፖለቲካ

Image
በመዝሙር ብቻ የምናውቀው ደረጀ ከበደ ወንድማችን ዘማሪ ደረጀ ከበደ በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየቱን መሠንዘር ከጀመረ ዓመት ሆኖታል። የፌስቡክ ታዳሚዎቹ፣ "ይኸ እርሱ አይደለም፣ በስሙ የሚነግዱ ግለሰቦች ናቸው" ወይም "ደረጀ እዚህ ዓይነት ውስጥ ባይጠላለፍ መልካም ነው" ወይም “ዶ/ር እንኳን የፌስቡክ ገጽህ ጓደኞች ልንሆን መድረክ ላይ ቆመህ ስታገለግል እንኳን ለማየት” ያልታደልን ነን እያሉ ነው። "እኔ ደረጀ ነኝ" ቢላቸውም፣ "በቪዲዮ ፊትህን አሳየንና፣ ድምጽህን አሰማንና እንጂ አናምንም" ብለዋል። ይኸ ሁሉ የሚያሳየው፣ ደረጀ ዓመታት ነጒደው እንኳ በሕዝብ ዘንድ ያሳደረው ፍቅር አለመደብዘዙን ነው። የእግዚአብሔር ጸጋ እውነትም አያረጅም፣ አያስረጅም! ደረጀ ከጅምሩ፣ “ፖስት የማደርጋቸው አስተያየቶችና ፅሁፎች የማይመቻችሁ ወገኖች ሰላማችሁ እንዳይደፈርስ በፍቅር ራሳችሁን ከገፁ ማግለል ትችላላችሁ” ብሏቸዋል። አባባሉ ግን ጥያቄ ያስነሳል። ለምሳሌ፣ መብትን በፍቅር ስለ መያዝ ምን ይነግረናል? መብት ዕንቅፋት ሲሆንስ? ( 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡9 ) በቀደመው ጥሪ ጸንቶ ማገልገል እንዴት ይቻላል? ( 1ኛ ቆሮንቶስ 12 ፤ ራእይ 2፡4፣5 ) ከስደት ዘመን ይልቅ በ “ሰላምና ነጻነት” ዘመን እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ግድ ነው። ደረጀ ፈር ቀዳጅ ነው፤ ዓይነተኛ ነው። ይህን በተለየ መንገድ የተረዳሁት ያሳተማቸውን ዘጠኝ አልበሞች በቅደም ተከተል ደርድሬ ለሰዓታት ባዳመጥኩ ጊዜ ነው። ረጅም “የክርስቲያን ጒዞ” እንደ መጓዝ ነው። ከርቀት ኮረብታን እንደ ማየት፣ አልፎ ወደ ኋላ መመልከት። ለምለም ሣር፣ ወንዝ፣ ቀጥሎ ምድረበዳ። ደስታ፣ ግራ መጋባት፤ የጠራ ሰማይ፣ የፀሐይ ሐሩር፣ ዶፍ፣ ነፋስ፣ ጠ...

የዘር ባንክ

Image
ስንዴ ጌትስ የዛሬ ሁለት ዓመት ቢል ጌትስ ኢትዮጵያን በጎበኘበት ወቅት ከጠ/ሚ ዐቢይ ጋር የተነሡት ፎቶ ነው። ከበስተ ኋላቸው የሚታየው የስንዴ እርሻ ነው። ቢል ጌትስ በጣም ሃብታም መሆን ብቻ ሳይሆን፣ በእርዳታ ስም የዓለም የሥልጣን ማዕከሎችን ለመቆጣጠር ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግ ሰው ነው። በጎ አድራጊ አይደለም ለማለት አይደለም። በጎ በማድረግ ውስጥ ግን ዓለምን በአምሳሉ መጠፍጠፍ ይዟል። አፍሪካውያን በብዛት ስለሚዋለዱ፣ ፈልሰው የአውሮጳን ደም እንዳይከልሱ ያለ ግለ ሰብ ነው። "አላስፈላጊ" ውርጃና ፅንስን መቆለፍን ይደግፋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች ላይ ትልቅ ተጽእኖ ማድረግ የተቻለው ሰው ነው። የእኛው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ያለ ቢል ጌትስ እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት ዲሬክተር መሆን ቀርቶ ደጁን አይረግጥም ነበር።  ህንዷ ሳይንቲስት ዶ/ር ቫንዳና ሺቫ፣ ስለ ጌትስ የሚገርም አሳብ የሠነዘረችበትን ለማዳመጥ ሊንኩ ። ትንሽ ሰጥቶ ገፈፋ ነው ብላለች። ለመሆኑ ጌትስ እና ዐቢይ ማንም አጠገባቸው ሳይኖር ምን ተባብለው ይሆን? ይህን አጣርቶ የሚነግረን አለ? ዐቢይ ማጋነን ስለሚያበዙ ቃላቸውን መተማመን ከቶ አይቻልም።  ጌትስ፣ በ2002 ዓም መለስ ዜናዊ ጋ መጥቶ፣ "ጂ ኤም ዖ" ስንዴ ድርቅና ረሓብ ላጠቃቸው አገሮች (እንደ ኢትዮጵያ ላሉት) ትልቅ ምርት ያስገኛል የሚል ሸቀጥ አራግፎ ነበር። 2,400 ገበሬዎች 100,000 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ መዝራት ጀምረው ነበር። አሳቡ ከጌትስ ነው፣ መሞከሪያው አፈሩ የኛ ነው። ዐቢይ፣ ስንዴ ከውጭ ማምጣት ትተን ውጭ አገር መላክ ጀምረናል ባሉን ወቅት፣ ስንት ሺህ ቶን ስንዴ ጂቡቲ ላይ እየተራገፈ ነበር። ያመረትነው ስንዴ ኮታው በጣም ከፍ ማለቱ እውነት ነው። እንኳን ደስ አለን! መለ...

Origins Of A Calendar

Image
Why Ethiopia Has Its Own Calendar: The Ancient Origins of the Ethiopian Calendar Girma A Demeke (PhD), Research & Publication Director, Institute of Semitic Studies Ethiopia will soon celebrate its New Year, marking a calendar transition distinct from the internationally adopted Gregorian system. This divergence includes both the method of calculating years and the fundamental structure of the day Specifically, from September 11/12 to 31 December, the Ethiopian calendar trails the Gregorian calendar by seven years, and by eight years from 1 January to September 10/11.  Additionally, while the Gregorian day commences at midnight, the Ethiopian day begins at dawn.  Explanations regarding the origins of these differences are often incomplete or convoluted by religious dogma, leaving the underlying mechanics poorly understood. A decade ago, we addressed this topic extensively in a book published in Amharic:  Girma A. Demeke. 2016. The Ethiopian Calendar (Text in Amhari...

የመደመር መዝሙር ምን ይመስል ይሆን?

Image
  የመደመር መዝሙር ምን ይመስል ይሆን? ክፍል አንድ ፦ እስከ 1966 ዓም ድረስ " የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ” ኢትዮጵያ ሆይ ! ደስ ይበልሽ ! ነበር። በማን ደስ ይበልሽ ? በአምላክሽ። በንጉሥሽ። አምላክሽ እና ንጉሥሽ አይነጣጠሉም፤ ሁለቱም ድል አድራጊ ናቸው። ሁለቱም አይደረስባቸውም። ንጉሥ አይከሰስም፤ ሰማይ አይታረስም። ብቻ ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ። ድህነትሽን ጉስቊልናሽን አታስቢ። ንጉሥሽ ክብርሽ ነው፤ በድህነትሽ አትፈሪ። አምላክ አለልሽ። ንጉሥ አለልሽ። በምድር ያጣሽውን በሰማይ ትካሺያለሽ። “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ ተባብረዋል አርበኞችሽ አይነካም ከቶ ነጻነትሽ ብርቱ ናቸውና ተራሮችሽ አትፈሪም ከጠላቶችሽ ድል አድራጊው ንጉሳችን ይኑርልን ለክብራችን” ነበር። [ ግጥም፦ ዮፍታሔ ንጉሤ። ዜማ ( አርመናዊው ) ኬቮርክ ናልባንዲያን ] ክፍል ሁለት ፦ ደርግ መጥቶ፦ የምን ንጉሥ ነው ? ወዲያልኝ አለ። የምን እግዚአብሔር ? ወዲያልኝ አለ። ከ 1967 ዓም እስከ 1984 ዓም የኢትዮጵያ ልጆች ባንድነት፦ " ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ " አልን። “ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ቅደሚ ፣ በኅብረሰባዊነት ፡ አብቢ ፡ ለምልሚ! ቃል ፡ ኪዳን ፡ ገብተዋል ፡ ጀግኖች ፡ ልጆችሽ ፣ ወንዞች ፡ ተራሮችሽ ፣ ድንግል ፡ መሬትሽ ፣ ለኢትዮጵያ ፡ አንድነት ፡ ለነጻነትሽ ፣ መሥዋዕት ፡ ሊኾኑ ፡ ለክብር ፡ ለዝናሽ ። ተራመጂ ፡ ወደፊት ፡ በጥበብ ፡ ጎዳና ፣ ታጠቂ ፡ ለሥራ ፡ ላገር ፡ ብልጽግና” አሉ። [ ግጥም፦ አሰፋ ገብረ ማርያም ተሰማ። ዜማ፦ ዳንኤል ዮሐንስ ...