በሌሎች ዓለማት ስላሉ ፍጥረቶች
ጠ/ሚ ዐቢይ፣ በ አይሁድ በ ክርስትና በ እስልምና ቲኦሎጂ፣ በ ኦሮሞ አንትሮፖሎጂ ስለ ሰባት ሰማያት እና በዚያ ስለሚገኙ ሌሎች ሰው መሰል ፍጥረቶች ከሰጡት ቃለ ምልልስ ቃል በቃል የተቀነጨበ። ". . . ከኃይማኖት አንፃር ደግሞ ያየህ እንደ ሆነ በተለይ ሦስቱ አብርሃሚክ (ከአብርሃም የወጡ ለማለት ነው) ኃይማኖቶች፣ አይሁድ እስልምናና ክርስትና ሦስቱም በዚህ ጉዳይ ይግባባሉ። ለምሳሌ አይሁድን ብትወስድ፣ በዕዝራ መጽሐፍ እንደ ሪፈረንስ (በእንግሊዝኛ ማጣቀሻ ለማለት ነው) ብንወስደው፣ ሰባቱ ሰማያት የማይታወቁ ሰማያት መኖራቸውን አይሁድ በእርግጠኝነት ያስተምራሉ፣ ያምናሉ በዚህ ሃሳብ። በእስልምናም ብዙ ስኮላርስ (በእንግሊዝኛ ምሑራን ለማለት ነው) በዚህ ረገድ ይናገራሉ። በተለይ ዶ/ር ዛኪር በጣም ታዋቂ ሙስሊም ስኮላር (ምሑር) ናቸው። እሳቸውን የቊርዐን አያን ሪፈር (በእንግሊዝኛ ጠቅሰው ለማለት ነው) አድርገው፣ ሰባት ሰማያት እንዳሉና በዚያ ውስጥ ፍጥረታት እንዳለ በእርግጠኝነት ይናገራሉ። በክርስትናም ስትወስድ፣ መጽሐፈ ኢዮብን፣ ኢዮብ 19፡15ን እንደ ምሳሌ ወስደው፣ ሠራተኞቼ ባርያዎቼ እንደ ባርያ ቆጠሩኝ የሚለው በተለይ እንግሊዝኛው "አልያን" ስለሚል፣ በእርግጠኝነት አለ ይላሉ። የኃይማኖት አስተምህሮዎች ይህን ይመስላሉ። ማስታወሻ ፦ በመጽሐፈ ዕዝራ ምእራፍ 10 “እንግዳ” የሚለው ከእስራኤል ሕዝብ ውጭ ስለ ተጋቡአቸው ሰዎች ነው። ኢዮብ 19፡15 “ቤተ ሰቦቼና ሴቶች ባሪያዎቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤ በዓይናቸውም እንደ እንግዳ ሆንሁ” ነው የሚለው። ሚንስትሩ “አልያን” (alien ኤልየን) ያሉት በእንግሊዝኛው “ኪንግ ጄምስ” መጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ላይ የተጠቀመ ቃል ነው። ትርጉሙ፦ በሌላ ዓለማት ስላሉ ፍጥረታት ሳይሆን፣ ኢዮብ፦ በመከራዬ ...