የዘር ባንክ

ስንዴ ጌትስ

የዛሬ ሁለት ዓመት ቢል ጌትስ ኢትዮጵያን በጎበኘበት ወቅት ከጠ/ሚ ዐቢይ ጋር የተነሡት ፎቶ ነው። ከበስተ ኋላቸው የሚታየው የስንዴ እርሻ ነው። ቢል ጌትስ በጣም ሃብታም መሆን ብቻ ሳይሆን፣ በእርዳታ ስም የዓለም የሥልጣን ማዕከሎችን ለመቆጣጠር ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግ ሰው ነው። በጎ አድራጊ አይደለም ለማለት አይደለም። በጎ በማድረግ ውስጥ ግን ዓለምን በአምሳሉ መጠፍጠፍ ይዟል። አፍሪካውያን በብዛት ስለሚዋለዱ፣ ፈልሰው የአውሮጳን ደም እንዳይከልሱ ያለ ግለ ሰብ ነው። "አላስፈላጊ" ውርጃና ፅንስን መቆለፍን ይደግፋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች ላይ ትልቅ ተጽእኖ ማድረግ የተቻለው ሰው ነው። የእኛው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ያለ ቢል ጌትስ እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት ዲሬክተር መሆን ቀርቶ ደጁን አይረግጥም ነበር። 

ህንዷ ሳይንቲስት ዶ/ር ቫንዳና ሺቫ፣ ስለ ጌትስ የሚገርም አሳብ የሠነዘረችበትን ለማዳመጥ ሊንኩ። ትንሽ ሰጥቶ ገፈፋ ነው ብላለች። ለመሆኑ ጌትስ እና ዐቢይ ማንም አጠገባቸው ሳይኖር ምን ተባብለው ይሆን? ይህን አጣርቶ የሚነግረን አለ? ዐቢይ ማጋነን ስለሚያበዙ ቃላቸውን መተማመን ከቶ አይቻልም። 

ጌትስ፣ በ2002 ዓም መለስ ዜናዊ ጋ መጥቶ፣ "ጂ ኤም ዖ" ስንዴ ድርቅና ረሓብ ላጠቃቸው አገሮች (እንደ ኢትዮጵያ ላሉት) ትልቅ ምርት ያስገኛል የሚል ሸቀጥ አራግፎ ነበር። 2,400 ገበሬዎች 100,000 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ መዝራት ጀምረው ነበር። አሳቡ ከጌትስ ነው፣ መሞከሪያው አፈሩ የኛ ነው። ዐቢይ፣ ስንዴ ከውጭ ማምጣት ትተን ውጭ አገር መላክ ጀምረናል ባሉን ወቅት፣ ስንት ሺህ ቶን ስንዴ ጂቡቲ ላይ እየተራገፈ ነበር። ያመረትነው ስንዴ ኮታው በጣም ከፍ ማለቱ እውነት ነው። እንኳን ደስ አለን! መለስ ያስጀመሩት ፕሮጄክት እንደ ሆነ ግን አልተገለጸም። ለምን ይሆን? ጌትስ፣ ሞንሳንቶ ከተባለ ድርጅት ጋር የንግድ ሽርክና እንዳለው አውቀናል? በአሜሪካ በ109,000 ሄክታር ባለቤትነቱ ጌትስ የመሬት ከበርቴዎች ቊንጮ መሆኑንስ? (የአዳማ ቆዳ ስፋት 3,000 ሄክታር ነው፤ የአዳማን 35 እጥፍ ማለት ነው።) ጌትስ ወደ ፊት ለሚያካሔደው ትልቅ የእርሻ ሥራ እየተዘጋጀ ነው። የአሜሪካ ገበሬዎች የእርሻ መሬት ግዢ በሦስት እጥፍ ተወድዶባቸው ተቸግረዋል። ምርጥ ዘር እየሰበሰበ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከተመረተው ምን ያህሉን ወደ ራሱ ዘር ባንክ ወስዶ ይሆን?

አገራችን አንድ ሃብቷ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር ባደላትና ምስኪን ገበሬዎቿ ያከማቹት የእርሻ ጥበብና ልዩ ልዩ የአዝርእት ዘር ነው። ባለፉት ዓመታት ከመሪዎቻችን አለማስተዋልና ዝርክርክነት የተነሳ ሆላንዶች የጤፍን ጠቀሜታ በንግድ ባለቤትነት ለመቆጣጠር ሞክረው ነበር። ከዓለም ዙሪያ ቡና ገዝቶ ቆልቶ በመሸጥ ሃብት ያፈራው የአሜሪካው ስታርበክስ፣ በ1999 ዓም፣ የአገራችንን ሲዳሞና ሐረር ቡና የንግድ ባለቤትነት (trademark) ቋምጦ ነበር፤ ከሸፈበት እንጂ። 

ዐቢይ እና ጌትስ የለበሱት ኮትና ሱሪ መመሳሰሉ ስለ መደመር ምን ይነግረን ይሆን? ዐቢይ፣ ጌትስ እጅ ላይ ስንት ፍሬ ስንዴ ቆጥረውለት ይሆን? ስንዴይቱን ኪሱ ከትቶ ሳይፈትሹት ከአገር ወጥቶ እንዳይሆን!


Comments

Popular posts from this blog

HaileSelassie's Band of Armenian Orphans

Blue Revolution

መስቀል ዘር የለውም

Dust In The Wind

የዐቢይ ወይስ የዓለም ጦርነት