ሕይወት ምሥጢር


የሕይወት ምሥጢር ቋጠሮ

አረንጉዋዴ ቸብቸቦ ውስጥ
የጽጌረዳ እምቡጥ
የወዳፍዋን ቋጠሮ
ሙጥሙጥ
በትንሹ ብቅ አድርጋ
ስታጒዋጒዋ
ስታጒዋጒዋ
ድብቅ ውበት።
እናይ ይሆን ፈንድታ
ስትቀይጥ ተቅላልታ
ቀለሙን
አረንጉዋዴነቱን።
ፍንዱ ተስጣቶላት
የውስጥ ሀብት
ዑደትዋ፣ ቅላትዋ
ተደራርቦውም እንጂ
የቀያይ ጆሮችዋ።
ማርያም ማርያም የምለው
ለውበት ልደት ነው፦
ለጽጌረዳዎች ውበት፤
ለሰው ልጆች ውበት፤
ለሕይወት ውበት
ድብቅ፤
የፍልቅቅ ፍልቅቅ
እንደጽጌረዳዋ ፈንድቶት
ተስጣቶት
እንዲያፍካካን
ሕይወታችንን ለውጦት።

~ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው“የተስፋ እግር ብረት” ገጽ 10-11
መስከረም 1969 ዓ.ም.፣ ብ/ሰ/ማ/ቤት፣ አ.አ.
ግጥሙ ለመጀመሪያ ጊዜ 19 June 2014 ኢትዮፕያንቸርች ላይ ታተመ።

Popular posts from this blog

HaileSelassie's Band of Armenian Orphans

The Prince and the Maharaja

Home of the Shy