አዲስ መንግሥት
አዋጅ! አዋጅ! "አካታች የሽግግር መንግሥት" ሊቋቋምልን ነው! እልል እንበል?
ከተለያየ ጎሳና ዓላማ ተነሥታችሁ "ሁሉን አካታች" እንዴት ልትሆኑ ትችላላችሁ? የለያያችሁም ያስተባበራችሁም ዐቢይ እንዴት ሊሆን ይችላል? ዐቢይ ሲወገድ ብትንትናችሁ እንደሚወጣ አስተውላችኋል? ወይስ ጊዜው ሲደርስ ልታስቡበት ነው? የየመንደራችሁ ሕዝብ እንዴት ያምናችኋል? ህወሓት ከዚህ የተለየ ምን አደረገ? በአማራ በኦሮሞ በደቡብ ስም ኢሕአዴግ አሰኝቶ አደል ህወሓት አዲሳባ የገባው? ታዲያስ? ትምህርት ቤት ገብታችሁ ከሆነ፣ ምን ዓይነት ትምህርት ቤት እንደ ተማራችሁ አላውቅም። ታሪክ የሚባል አንብባችሁ የምታውቁ አትመስሉም። ደሃው ሕዝብ ለናንተ ሥልጣን መያዝ ለምን ፍዳውን ይቁጠር? ማናችሁም የህወሓትን ወይም የሻብያን ያክል የጦር ድርጅትና ልምድ የላችሁም። ዐቢይ ሲወገድ ያው ከህወሓት/ሻብያ ኪስ ገቢ ናችሁ።