ጠ/ሚ ዐቢይ፣ በ አይሁድ በ ክርስትና በ እስልምና ቲኦሎጂ፣ በ ኦሮሞ አንትሮፖሎጂ ስለ ሰባት ሰማያት እና በዚያ ስለሚገኙ ሌሎች ሰው መሰል ፍጥረቶች ከሰጡት ቃለ ምልልስ ቃል በቃል የተቀነጨበ።
". . . ከኃይማኖት አንፃር ደግሞ ያየህ እንደ ሆነ በተለይ ሦስቱ አብርሃሚክ (ከአብርሃም የወጡ ለማለት ነው) ኃይማኖቶች፣ አይሁድ እስልምናና ክርስትና ሦስቱም በዚህ ጉዳይ ይግባባሉ። ለምሳሌ አይሁድን ብትወስድ፣ በዕዝራ መጽሐፍ እንደ ሪፈረንስ (በእንግሊዝኛ ማጣቀሻ ለማለት ነው) ብንወስደው፣ ሰባቱ ሰማያት የማይታወቁ ሰማያት መኖራቸውን አይሁድ በእርግጠኝነት ያስተምራሉ፣ ያምናሉ በዚህ ሃሳብ። በእስልምናም ብዙ ስኮላርስ (በእንግሊዝኛ ምሑራን ለማለት ነው) በዚህ ረገድ ይናገራሉ። በተለይ ዶ/ር ዛኪር በጣም ታዋቂ ሙስሊም ስኮላር (ምሑር) ናቸው። እሳቸውን የቊርዐን አያን ሪፈር (በእንግሊዝኛ ጠቅሰው ለማለት ነው) አድርገው፣ ሰባት ሰማያት እንዳሉና በዚያ ውስጥ ፍጥረታት እንዳለ በእርግጠኝነት ይናገራሉ። በክርስትናም ስትወስድ፣ መጽሐፈ ኢዮብን፣ ኢዮብ 19፡15ን እንደ ምሳሌ ወስደው፣ ሠራተኞቼ ባርያዎቼ እንደ ባርያ ቆጠሩኝ የሚለው በተለይ እንግሊዝኛው "አልያን" ስለሚል፣ በእርግጠኝነት አለ ይላሉ። የኃይማኖት አስተምህሮዎች ይህን ይመስላሉ።
ማስታወሻ፦ በመጽሐፈ ዕዝራ ምእራፍ 10 “እንግዳ” የሚለው ከእስራኤል ሕዝብ ውጭ ስለ ተጋቡአቸው ሰዎች ነው። ኢዮብ 19፡15 “ቤተ ሰቦቼና ሴቶች ባሪያዎቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤ በዓይናቸውም እንደ እንግዳ ሆንሁ” ነው የሚለው። ሚንስትሩ “አልያን” (alien ኤልየን) ያሉት በእንግሊዝኛው “ኪንግ ጄምስ” መጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ላይ የተጠቀመ ቃል ነው። ትርጉሙ፦ በሌላ ዓለማት ስላሉ ፍጥረታት ሳይሆን፣ ኢዮብ፦ በመከራዬ ሰዓት የቅርቤ ናቸው ያልኳቸው የቤቴ ሰዎች እንደ ባዳ ወይም እንደ ባይተዋር ቆጠሩኝ ማለቱ ነው።
ወደ ታሪክ ታሪክ መጽሐፍት ደግሞ ብንወስድ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ
ጥንታዊ ጽሑፎች ለምሳሌ መጽሐፈ ኄኖክን ብትወስድ፣ እ እ ዜና እስክንድርን ብትወስድ፣ ምሥጢረ ዜና መጽሐፍትን ብትወስድ፣ በእነዚህ ላይ ሳይዛቸውም (በእንግሊዝኛ
ቁመናቸው ለማለት ነው) ጭምር ጭንቅላታቸው ትልቅ ምን እንደሚመስሉ ሁሉ ተጽፏል። ቀደምት የኢትዮጵያ የኛ ሲስተርስ (በእንግሊዝኛ መነኮሳት/እህቶች) ጽፈውታል (እነ ማንን ማለታቸው እንደ ሆነ አልተጠየቁም)። ወደ ቦረና አካባቢ ጉጂ አካባቢ ደግሞ ስትሄድ በአስትሮኖሚ ብዙ በጣም የሚነገር ነገር ስላለ፣ እነርሱም ከዘመን
አቆጣጠር ጀምሮ በሌላ ዓለም ስላለው ፍጥረት የሚናገሩበት በጣም ብዙ አፈ ታሪኮች አሉ። እና፣ በታሪክ ይህን መልክ አለው። በኃይማኖት
በእርግጠኝነት ይናገራሉ። ሳይንስም የሉም አይልም፣ አንዴ ያገዝፋቸዋል፣ አንዴ ያሳንሳቸዋል። በተለየ ዶ/ር ሚካኤል በቅርቡ በፃፈው
መጽሐፍ ላይ እስካሁን ዩፎ (UFO) ነበር የሚባሉት "አንአይደንቲፋይድ ፍላይንግ ኦብጀክት" ነበሩ። እርሱ ግን “ዩ”ን ቀይሮ “አይ” አድርጎታል፣ "አይደንቲፋይድ" ናቸው፤ "አይደንቲፋይድ ፍላይንግ ኦብጀክት" ናቸው ብሎ ነው የቀረበው። ለዚያ ሳይንሳዊ መረጃ ማቅረብ አልቻለም። በኔ
ግምት ዩኒቨርስ (ዓለማት) በጣም ትልቅ ስለ ሆነ በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ የተለያዩ ፍጥረታት ሊኖሩ ይችላሉ። ግን እኛ ኮምሬንድ (በእንግሊዝኛ
መረዳት ለማለት ነው) ማድረግ የምንችልበት ደረጃ ደርሰናል ማለት አይደለም . . . "
[ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ]
Comments
Post a Comment