Posts

ኢትዮጵያ

Image
  ይ ቺ  ና ት  የ ኔ  ም ድ ር በ   ፍ ቅ ሬ  ቶ ሎ ሳ ግን እኮ እዚህም ኢዮሄ! እልልሻለሁ፤ አለቅሥልሻለሁ ለብቻዬ ከመላው ምድረገጽ ለሥቃይ፣ ለርሀብ፣ ለምን? ለምን? ተመረጠች ኢትዮጵያዬ! በኃጢዓትዋ ነው ይሉኛል ቄሱ፤ መልሳቸው አንጀቴን ላያረካ ኃጢዓትሽ ይብስ ይሆን ከአውሮፓና ከአሜሪካ? እግዜር ስለሚያፈቅራት ነው የሚቀጣት ይላሉ ቄሱ አባትም የሚቀጣው የገዛ ልጁን ብቻ ነው የሚወደውን እንደራሱ ሌሎቹን የማይቀጣቸው ስላይደሉ ነው የሱ። እሥራኤል እግዜር የመረጠው ሕዝቡ ሆኖት ባምላኩ ላይ ስላመፀ፣ በርሀብ፣ በቸነፈር፣ በጦርነት ቀጥቶት፣ በመላው ዓለም በታትኖት ኋላ ግን ሕዝበ እሥራኤል ቢፀፀት ጥፋተኛነቱን ተቀብሎ እንደገና ሠብሥቦ ነፍሥ ዘራበት፣ እንደሌላው አልጣለውም ጥሎ ኢትዮጵያም እግዚኦ ካለች፣ ይታረቃታል በቃሽ ብሎ። ፖለቲከኛውንም ስጠይቀው የራሱን መልሥ ይሠጠኛል በመንግሥት፣ በተፈጥሮና በአስተራረስ ጥፋት ነው ይለኛል። ባለታሪኩንም ባናግረው “ካክሱም በፊት ያለውንኳ ብንተወው ተነግሮ ስለማይጨረስ ካክሱም መመሥረት አንሥቶ እስከጣሊያን ወረራ ድረሥ የኢትዮጵያን ታሪክ ብንመረምረው ባለፈው ሃምሣ ዓመት ብቻ * ከውጭ ወራሪ ጋር መተላለቅ፣ ርሥበርሥ መተራረድ ነው ባለም የሌለው አቻ የደም መፍሠሥ ታሪክ ነው ታሪክዋ የኢትዮጵያ ታዲያ መቸ ሠላም አግኝታ ትሻሻል? ይለኛል የታሪኩ ባለሞያ። መንሥኤው ሰው-ሠራሽ ይሁን የእግዜር ቊጣ፣ ወይም የተፈጥሮ ሐቊ ተርበሻል፣ ተራቊተሻል፣ ደምተሻል ኢትዮጵያዬ ምክንያት ቢደረደር አይበጅም ዘንድሮ። እኔ ልጅሽ ግን አምናለሁ፣ ይኸ ቀውጢ ቀንሽ ተሽሮ በጥጋብ፣ በብልጽግና፣ በፍቅር፣ በሠላም ተቀይሮ ዛሬ ለርሀብና ለጦርነት ተጋልጠሽ እንደተዋረድሽ፣ ነገ አንቺነትሽ ተከብሮ አንቺ ለመላው ...

ወሬ

Image
  ድሮን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ግቢ ላይ ተተኩሶ 2 ሰዎች ሞቱ የሚል ዜና ባለፈው ሳምንት ተሰምቶ ነበር። የ ዐቢይ አስተዳደር ምላሽ ምን ነበር? ዝም። ከሁለት ቀናት በፊት አዲሳባ በድሮን ተመታች የሚል ዜና ተጨምሮ ተናፈሰ። የኢትዮጵያ መሪ ምላሽ ምን ነበር? ዝም። እርግጥ፣ ያልተመዘገበ ድሮን ጨርሶ እንዳይበርር ትእዛዝ አውጥቷል። የኤርትራን ቆንስላ ዘግቷል። የግብፅን ዲፕሎማት አባርሯል። ለኢትዮጵያ በጎ አስበው የማያውቁ ሁለቱ ወዳጆች አፃፋውን መልሰዋል። የ ዐቢይ አስተዳደር ባለፈውም ባሁኑም ጦርነት ያላወቀበት ጉዳይ የሕዝብን አመኔታና የዓለም ማኅበረ ሰብን አስተያየት እንዴት መማረክ እንደሚቻል ነው። ዝምታ ወርቅ አይደለም። የሰው ልብ የሚያምነው የተነዛው ወሬ እውነት አለመሆኑን አይደለም። የሰሚ ልብ የሚሰማው፦ ከትንሿ ኤርትራ በሕዝብ ቊጥርና በሃብት ክምችት እጅግ የምትበልጠው ኢትዮጵያ አቅመ ቢስ ሆና መታየቷን ነው። ዐቢይ ይህን ዋነኛ ቊምነገር ካለፈው ስሕተት ተምረው ዛሬም ለይተው አላወቁም። በደፈናው ብቻ በድንፋታ፦ እኛ እኮ 130 ሚሊዮን ሕዝብ አለን ይላሉ። ወይም፦ ከመቶ በላይ የጦር አውሮፕላኖች። ማንም አይበግረንም። ይሞክረንና ያገኛታል ዓይነት ፉከራ። ጉዳዩ ግን የዓለም ማኅበረ ሰብን አእምሮ ማ ረታ ነው። ከሁሉ የሚብሰው ግን። የኢትዮጵያን ሕዝብ አመኔታ ማጣት ነው። ሕዝቡ ኑሮ እጅግ መርሮታል። አጥነቱን የሚግጡትን ወሮበሎች ዐቢይ ንክች ማድረግ አልፈለጉም፤ አልቻሉም። ምክንያቱ፣ ወሮበሎቹ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ናቸው።  የአፄ ኃይለሥላሴም የ መንግሥቱ ኃይለማርያምም የ መለስ ዜናዊም መንግሥት የፈረሰው የሕዝብ ልብ ስለ ከዳው ነው። የዐቢይ ብልጽግና አሸሼ ገዳዎ፣ ልብስ እንጀራ ህክምና መኖሪያ ሥራ መሆን አልቻለም። እንዲያው በድፍኑ ወደ ...

Dust In The Wind

Image
ብናኝ አቧራ ነን ለሴኮንድ ብቻ ዐይኔን ጨፍኜ ሴኮንዱ ከምኔው በንኖ ሄዷል ምኞቴ እያየሁት ከመቅጽበት አልፏል— ይገርማል ብናኝ ነው ሁሉ ብናኝ፣ አቧራ ነው ድግግሞሽ ማለቂያ የለሽ ድግግሞሽ ውቅያኖስ ላይ ጠብታ ነው አንድባንድ ጥረታችን ሁሉ ልብ አንልም ይንኮታኮታሉ ብናኝ፣ በነፋስ ፊት ብናኝ ነን ብናኝ አቧራ ነን ምንም መቸም አትጠብቅ ከምድር-ሰማይ በቀር፣ የለምና ‘ሚዘልቅ ሁሉ አላፊ ነው ሃብት ቢትረፈረፍ አይሸምትም ደቂቅ ትቢያ ነው፣ ሁሉ ትቢያ ነፋስ በነፋስ ፊት ሁሉም ብናኝ አቧራ ነው ገጣሚ፦ (በእንግሊዝኛ) ኬሪ ሊቭግረን (1969 ዓም) ተርጓሚ፦ © ምትኩ አዲሱ ፣ 2015 ዓም ኬሪ፣ ይህን ቅኔ ካሳተመ ከ2 ዓመት በኋላ የክርስቶስ ተከታይ ሆኗል። Lyrics: Kerry Livgren (1977) Translation ( አማርኛ Amharic): Mitiku Adis u (2022) Dust In The Wind Well, I close my eyes Only for a moment and the moment's gone All my dreams Oh, they pass before my eyes with curiosity Dust in the wind All they are is dust in the wind Same old song Just a drop of water in an endless sea All we do Crumbles to the ground, though we refuse to see Dust in the wind (oh) All we are is dust in the wind, ay Oh, oh Now don't hang on Nothin' lasts forever but the earth and sky Well, it slips away Oh, all your money won't another minute buy,...

Blue Revolution

Image
  There is now a  Brigade N'hamedu  (this time to wage a "blue" revolution) operating out of Israel, the goal of which is to oust the 80-year-old Isaias Afwerki from power and establish a "democratic" state. Afwerki has been the sole ruler since "Ethiopia-colonised" Eritrea got its independence in 1993.   Brigade N'hmedu's leader is Beyene Gerezgiher . Beyene currently resides in Ethiopia's capital Addis Ababa.   The brigade, we are told, now has a 51-member international council.  A couple of million Eritreans currently live in exile (total population in Eritrea proper is less than 4 million (2026 World Population Review estimate). Recently, those in Israel were threatened with deportation as protests in support of the "blue revolution" turned into violent clashes with the pro-Isaias group. Street clashes between the opposition and supporters of the current regime are now the pattern everywhere.  Interestingly, the Trump Admini...

መስቀል ዘር የለውም

Image
ደግሞ የመስቀል ደመራ ቀን ደረሰ። የኢትዮጵያ መንደሮች ከተሞች ቤቶች በያሉበት ተሰባሰቡ። የሰላም ምኞት፣ የተስፋ የምሥጋና እሳት አጋዩ። ሁሉም በያለበት ተጠጋግቶ ቆመ። እንደ አንድ ቤተ ሰብ ቆመ። እንደ አንድ አገር ቆመ። ሴት ወንድ ሳይል። ሕፃን ሽማግሌ ሳይል። ሃብታም ደሃ ሳይል። ዘር ሳይለይ። ቋንቋ ሳይለይ። ኃይማኖት ሳይለይ።  የእሳት ብርሃን ኃይማኖት የለውም፤ ክልል የለውም፤ ዘር የለውም። መስቀል ሰላም ነው። መስቀል የእግዚአብሔር ኃይል ነው። መስቀል እርቅ ነው፦ በሰውና በአምላኩ መሓል፤ ሰው ከራሱ ጋር፤ ሰው ከባላጋራው ጋር፤ ሰው ከምድር አየሩ ሰማዩ ከፍጥረት ሁሉ ጋር።  መስቀል ደመራ ደረሰ። ሕዝብ ሁሉ ፊቱን ወደ እሳት፤ ወደ ብርሃን አዞረ። ፊቱን ወደ ብርሃን ተስፋ አዙሮአልና ፊቱ አበራ። እርስ በርስ ተያየ። ጭለማው ሸሸ። ቆፈን ሥፍራ አጣ። ሰው እርስ በርስ ተሟሟቀ። እግዚአብሔር ምድራችንን ይባርክ። ጭለማውን ያግድ። ተስፋና ሕይወትን የሚያጨልምን ያንድድ። [ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የተላለፈ መልእክት] ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ። የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል። ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ አደባባይ ይተምበታል። ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው። በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ። በድጋሚ መልካም በዓል ይሁን። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም