Posts

መዝሙር እና ፖለቲካ

Image
በመዝሙር ብቻ የምናውቀው ደረጀ ከበደ ወንድማችን ዘማሪ ደረጀ ከበደ በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየቱን መሠንዘር ከጀመረ ዓመት ሆኖታል። የፌስቡክ ታዳሚዎቹ፣ "ይኸ እርሱ አይደለም፣ በስሙ የሚነግዱ ግለሰቦች ናቸው" ወይም "ደረጀ እዚህ ዓይነት ውስጥ ባይጠላለፍ መልካም ነው" ወይም “ዶ/ር እንኳን የፌስቡክ ገጽህ ጓደኞች ልንሆን መድረክ ላይ ቆመህ ስታገለግል እንኳን ለማየት” ያልታደልን ነን እያሉ ነው። "እኔ ደረጀ ነኝ" ቢላቸውም፣ "በቪዲዮ ፊትህን አሳየንና፣ ድምጽህን አሰማንና እንጂ አናምንም" ብለዋል። ይኸ ሁሉ የሚያሳየው፣ ደረጀ ዓመታት ነጒደው እንኳ በሕዝብ ዘንድ ያሳደረው ፍቅር አለመደብዘዙን ነው። የእግዚአብሔር ጸጋ እውነትም አያረጅም፣ አያስረጅም! ደረጀ ከጅምሩ፣ “ፖስት የማደርጋቸው አስተያየቶችና ፅሁፎች የማይመቻችሁ ወገኖች ሰላማችሁ እንዳይደፈርስ በፍቅር ራሳችሁን ከገፁ ማግለል ትችላላችሁ” ብሏቸዋል። አባባሉ ግን ጥያቄ ያስነሳል። ለምሳሌ፣ መብትን በፍቅር ስለ መያዝ ምን ይነግረናል? መብት ዕንቅፋት ሲሆንስ? ( 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡9 ) በቀደመው ጥሪ ጸንቶ ማገልገል እንዴት ይቻላል? ( 1ኛ ቆሮንቶስ 12 ፤ ራእይ 2፡4፣5 ) ከስደት ዘመን ይልቅ በ “ሰላምና ነጻነት” ዘመን እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ግድ ነው። ደረጀ ፈር ቀዳጅ ነው፤ ዓይነተኛ ነው። ይህን በተለየ መንገድ የተረዳሁት ያሳተማቸውን ዘጠኝ አልበሞች በቅደም ተከተል ደርድሬ ለሰዓታት ባዳመጥኩ ጊዜ ነው። ረጅም “የክርስቲያን ጒዞ” እንደ መጓዝ ነው። ከርቀት ኮረብታን እንደ ማየት፣ አልፎ ወደ ኋላ መመልከት። ለምለም ሣር፣ ወንዝ፣ ቀጥሎ ምድረበዳ። ደስታ፣ ግራ መጋባት፤ የጠራ ሰማይ፣ የፀሐይ ሐሩር፣ ዶፍ፣ ነፋስ፣ ጠ...

የዘር ባንክ

Image
ስንዴ ጌትስ የዛሬ ሁለት ዓመት ቢል ጌትስ ኢትዮጵያን በጎበኘበት ወቅት ከጠ/ሚ ዐቢይ ጋር የተነሡት ፎቶ ነው። ከበስተ ኋላቸው የሚታየው የስንዴ እርሻ ነው። ቢል ጌትስ በጣም ሃብታም መሆን ብቻ ሳይሆን፣ በእርዳታ ስም የዓለም የሥልጣን ማዕከሎችን ለመቆጣጠር ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግ ሰው ነው። በጎ አድራጊ አይደለም ለማለት አይደለም። በጎ በማድረግ ውስጥ ግን ዓለምን በአምሳሉ መጠፍጠፍ ይዟል። አፍሪካውያን በብዛት ስለሚዋለዱ፣ ፈልሰው የአውሮጳን ደም እንዳይከልሱ ያለ ግለ ሰብ ነው። "አላስፈላጊ" ውርጃና ፅንስን መቆለፍን ይደግፋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች ላይ ትልቅ ተጽእኖ ማድረግ የተቻለው ሰው ነው። የእኛው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ያለ ቢል ጌትስ እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት ዲሬክተር መሆን ቀርቶ ደጁን አይረግጥም ነበር።  ህንዷ ሳይንቲስት ዶ/ር ቫንዳና ሺቫ፣ ስለ ጌትስ የሚገርም አሳብ የሠነዘረችበትን ለማዳመጥ ሊንኩን እዚህ ተመልከቱ። ትንሽ ሰጥቶ ገፈፋ ነው ብላለች። ለመሆኑ ጌትስ እና ዐቢይ ማንም አጠገባቸው ሳይኖር ምን ተባብለው ይሆን? ይህን አጣርቶ የሚነግረን አለ? ዐቢይ ማጋነን ስለሚያበዙ ቃላቸውን መተማመን ከቶ አይቻልም።  ጌትስ፣ በ2002 ዓም መለስ ዜናዊ ጋ መጥቶ፣ "ጂ ኤም ዖ" ስንዴ ድርቅና ረሓብ ላጠቃቸው አገሮች (እንደ ኢትዮጵያ ላሉት) ትልቅ ምርት ያስገኛል የሚል ሸቀጥ አራግፎ ነበር። 2,400 ገበሬዎች 100,000 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ መዝራት ጀምረው ነበር። አሳቡ ከጌትስ ነው፣ መሞከሪያው አፈሩ የኛ ነው። ዐቢይ፣ ስንዴ ከውጭ ማምጣት ትተን ውጭ አገር መላክ ጀምረናል ባሉን ወቅት፣ ስንት ሺህ ቶን ስንዴ ጂቡቲ ላይ እየተራገፈ ነበር። ያመረትነው ስንዴ ኮታው በጣም ከፍ ማለቱ እውነት ነው። እንኳን...

Origins Of A Calendar

Image
Why Ethiopia Has Its Own Calendar: The Ancient Origins of the Ethiopian Calendar Girma A Demeke (PhD), Research & Publication Director, Institute of Semitic Studies Ethiopia will soon celebrate its New Year, marking a calendar transition distinct from the internationally adopted Gregorian system. This divergence includes both the method of calculating years and the fundamental structure of the day Specifically, from September 11/12 to 31 December, the Ethiopian calendar trails the Gregorian calendar by seven years, and by eight years from 1 January to September 10/11.  Additionally, while the Gregorian day commences at midnight, the Ethiopian day begins at dawn.  Explanations regarding the origins of these differences are often incomplete or convoluted by religious dogma, leaving the underlying mechanics poorly understood. A decade ago, we addressed this topic extensively in a book published in Amharic:  Girma A. Demeke. 2016. The Ethiopian Calendar (Text in Amhari...

የመደመር መዝሙር ምን ይመስል ይሆን?

Image
  የመደመር መዝሙር ምን ይመስል ይሆን? ክፍል አንድ ፦ እስከ 1966 ዓም ድረስ " የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ” ኢትዮጵያ ሆይ ! ደስ ይበልሽ ! ነበር። በማን ደስ ይበልሽ ? በአምላክሽ። በንጉሥሽ። አምላክሽ እና ንጉሥሽ አይነጣጠሉም፤ ሁለቱም ድል አድራጊ ናቸው። ሁለቱም አይደረስባቸውም። ንጉሥ አይከሰስም፤ ሰማይ አይታረስም። ብቻ ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ። ድህነትሽን ጉስቊልናሽን አታስቢ። ንጉሥሽ ክብርሽ ነው፤ በድህነትሽ አትፈሪ። አምላክ አለልሽ። ንጉሥ አለልሽ። በምድር ያጣሽውን በሰማይ ትካሺያለሽ። “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ ተባብረዋል አርበኞችሽ አይነካም ከቶ ነጻነትሽ ብርቱ ናቸውና ተራሮችሽ አትፈሪም ከጠላቶችሽ ድል አድራጊው ንጉሳችን ይኑርልን ለክብራችን” ነበር። [ ግጥም፦ ዮፍታሔ ንጉሤ። ዜማ ( አርመናዊው ) ኬቮርክ ናልባንዲያን ] ክፍል ሁለት ፦ ደርግ መጥቶ፦ የምን ንጉሥ ነው ? ወዲያልኝ አለ። የምን እግዚአብሔር ? ወዲያልኝ አለ። ከ 1967 ዓም እስከ 1984 ዓም የኢትዮጵያ ልጆች ባንድነት፦ " ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ " አልን። “ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ቅደሚ ፣ በኅብረሰባዊነት ፡ አብቢ ፡ ለምልሚ! ቃል ፡ ኪዳን ፡ ገብተዋል ፡ ጀግኖች ፡ ልጆችሽ ፣ ወንዞች ፡ ተራሮችሽ ፣ ድንግል ፡ መሬትሽ ፣ ለኢትዮጵያ ፡ አንድነት ፡ ለነጻነትሽ ፣ መሥዋዕት ፡ ሊኾኑ ፡ ለክብር ፡ ለዝናሽ ። ተራመጂ ፡ ወደፊት ፡ በጥበብ ፡ ጎዳና ፣ ታጠቂ ፡ ለሥራ ፡ ላገር ፡ ብልጽግና” አሉ። [ ግጥም፦ አሰፋ ገብረ ማርያም ተሰማ። ዜማ፦ ዳንኤል ዮሐንስ ...