Posts

በሽታ ነው

በሽታው እውነት ነው! ፌዴራል መንግሥት ሰኔ 21/2013 ዓ.ም. በራሱ ተነሳሽነት በትግራይ ተኲስ አቊም አድርጌአለሁ ብሎናል። የአዝመራ ጊዜ እንዳያልፍ፣ ፀጥታ ማስከበር ያስከተለው ወጪ እና የውጭ መንግሥታት ጫና ለውሳኔው ምክንያት ተደርገው ቀርበዋል። ፌዴራል መንግሥት እውነቱን ሁሉ ይንገረን አይንገረን ማወቅ አይቻልም። በተለያዩ ጊዜአት ወቅታዊ መረጃ ለሕዝብ አለማቅረቡ ያሰለቸ ጒዳይ ነው። ለምሳሌ፣ "ህወሓት ማለት በንፋስ ላይ እንደ ተበተነ ዱቄት ነው" እንዳልተባልን፣ ህወሓት እዚህ ታየ፣ እዚያ ገባ ወሬ እየተናፈሰ ፌዴራል መንግሥት ጭጭ ማለቱ ትርጒም የለውም። እርግጥ ነው፣ ህወሓት የሚታወቀው አሳች ወሬ በመንዛት ነው። ሕዝብ አመኔታ እንዲኖረው ካስፈለገ ግን፣ ለህወሓት ተስፋፊ ወሬ፣ በተለይ በውጭው ዓለም ዜና አውታሮች ለሚሠራጩ መረጃ አልባ ወሬዎች፣ አፀፋ መስጠት ግድ ነው። የአገራችን በሽታ እውነት ነው! እውነት አለመነጋገር ነው። ውሸቱን የሚለይ መረጃ ማጣት ወይም አለመፈለግ ነው። ኤስ ቢ ኤስ አውስትራልያ አማርኛ ራዲዮ ሦስት ኢትዮጵያውያንን ስለ ተኲስ አቊሙ አነጋግሯል። ያቀረበላቸው ጥያቄ፦ "የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል ተኲስ ማቆም ዕወጃ ፋይዳ ምንድነው?" የሚል ሲሆን፣ ምላሻቸውን ቆንጽሎ እንዲህ ለጥፎታል፦ “የረጅም ጊዜ አዎንታዊ ተፅዕኖው ወደፊት የሚታይ ሆኖ፤ መንግሥት የወሰደውን የአንድ ወገን ተኩስ አቁም የምመለከተው በአዎንታዊ ጎኑ ነው። የመንግሥትን ሆደ ሰፊነትና ቻይነት የሚያሳይ መልካም ራዕይ ያለው ውሳኔ ነው።” ~ አቶ አዳሙ ተፈራ “የፌዴራል መንግሥቱ ተኩስ አቁሜያለሁ ብሎ ቢያውጅም፤ የእርዳታ ክልከላው፣ የቴሌኮም ክልከላው፣ ድልድይ መስበሩና ባንክ እንዳይንቀሳቀስ ማድረጉ አልቆመም። ጦርነቱ መልኩን ቀየረ እንጂ ...

ወዳጆች

Image
የታማኝ ወዳጆች መከዳዳት ባንድ አገር የሚተማመኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ። ከነዚህም አንደኛው በሀብቱ የገነነ በሽምግልናው የተከበረ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እየሠራ ከሚያፈራው ከዕለት ምግቡ ካመት ልብሱ የሚተርፈው ገንዘቡን እየወሰደ ባደራ ስም አኑርልኝ እያለ ለባለጸጋው የሚሰጥ ነበረ። ያም ታማኝ መሳዩ ሽማግሌ ያደራውን ገንዘብ እየተቀበለ ሲያስቀምጥለት ቆይቶ አንድ ቀን ባለ ገንዘቡ ለዕለት ችግሩ ካኖረው ሒሳብ ላይ  ጥቂት እንዲሰጠው ቢጠይቀው ምን ሰጠኸኝና ትጠይቀኛለህ አላየሁም ብሎ ጨርሶ ካደው፤ እየተመላለሰ በማሳዘን ቢለምነውም አላዘነለትም፣ አልራራለትም። ቁርጡን ካወቀ በኋላ ላገሩ ዳኛ ክስ ለማቅረብ ሄዶ አመለከተ፤ ዳኛውም ስትሰጠው ያየህ ምስክር የሚሆን ሰው አለህን ብሎ ቢጠይቀው ከኔና ከሱ በቀር ማንም ሰው አልነበረም አለው። እንግዲያስ እኔ እጠይቅልሃለሁና ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሰህ እንድትመጣ ብሎ አስታወቀው። ብልኁ ዳኛ አደራ አስቀማጩን ሰው ጠርቶ፣ አሁን ያስጠራሁህ እኔ በድንገት ከዚህ አገር ከሹመቴ ተሽሬ መሄዴ ነው፤ ብጠይቅ ባስጠይቅም ታማኝ ሽማግሌ ባገር ያለኸው አንተ መሆንህን ሰማሁ፡ ስለዚህ ዕቃዬንና ያለኝን ገንዘቤን በሙሉ አንድ ጊዜ አንሥቼ ለመሄድ ስለማይቻለኝ አንተ ዘንድ እንድታስቀምጥልኝና በየጊዜው ሰው ስልክ እንድትሰጥልኝ እለምንሃለሁ አለው። ሽማግሌውም እንግዲህ ይህ ያገር ዳኛ ትልቅ ሰው ስለ ሆነ ባደራ የሚያስቀምጠው ገንዘብ በብዙ ሺ የሚቆጠር ዕቃውም ካይነቱ ብዛት ጋራ የበረከተ ይሆናልና ይኸን ተቀብዬ አላየሁም ብዬ ባለሀብት ባለገንዘብ እሆናለሁ ብሎ ደስ አለውና ለዳኛው እሺ ጌታዬ ሲል መልስ ሰጠው። ከሦስት ቀንም በኋላ ያ ባለገንዘብ ለዳኛው በቀጠሮዬ መጥቻለሁ ብሎ አመለከተው። እንግዲህ ሂድና አንዳችም ነገር ሳትጨምር ባገሩ ዳኛ ልከስህ ነ...

3

Image
 

ዜማ

Image
  ወፍ እና ማለዳ እንኳንስ ችግኙ፥ ሰዎች የተከሉት ሥር ይይዝ ነበረ፥ አዕዋፍ የዘሩት። ዘንድሮ ግን ወፎች፥ እንኳንስ ሊዘሩ ናፍቆኛል ማለዳ፥ መስማት ሲዘምሩ። ወፎች ከማለዳ - በምን ተቃቃሩ?! ፅልመቱ ሲገፈፍ - እንዳላበሰሩ፤ ማዜም ተስኗቸዉ - ተዘግቶ ጀንበሩ ወደሚነጋበት - ወዴትስ በረሩ?! ~ አብደላ ዕዝራ pic credit: pinterest.com

ኢትዮጵያ

Image
  ይ ቺ  ና ት  የ ኔ  ም ድ ር በ   ፍ ቅ ሬ  ቶ ሎ ሳ ግን እኮ እዚህም ኢዮሄ! እልልሻለሁ፤ አለቅሥልሻለሁ ለብቻዬ ከመላው ምድረገጽ ለሥቃይ፣ ለርሀብ፣ ለምን? ለምን? ተመረጠች ኢትዮጵያዬ! በኃጢዓትዋ ነው ይሉኛል ቄሱ፤ መልሳቸው አንጀቴን ላያረካ ኃጢዓትሽ ይብስ ይሆን ከአውሮፓና ከአሜሪካ? እግዜር ስለሚያፈቅራት ነው የሚቀጣት ይላሉ ቄሱ አባትም የሚቀጣው የገዛ ልጁን ብቻ ነው የሚወደውን እንደራሱ ሌሎቹን የማይቀጣቸው ስላይደሉ ነው የሱ። እሥራኤል እግዜር የመረጠው ሕዝቡ ሆኖት ባምላኩ ላይ ስላመፀ፣ በርሀብ፣ በቸነፈር፣ በጦርነት ቀጥቶት፣ በመላው ዓለም በታትኖት ኋላ ግን ሕዝበ እሥራኤል ቢፀፀት ጥፋተኛነቱን ተቀብሎ እንደገና ሠብሥቦ ነፍሥ ዘራበት፣ እንደሌላው አልጣለውም ጥሎ ኢትዮጵያም እግዚኦ ካለች፣ ይታረቃታል በቃሽ ብሎ። ፖለቲከኛውንም ስጠይቀው የራሱን መልሥ ይሠጠኛል በመንግሥት፣ በተፈጥሮና በአስተራረስ ጥፋት ነው ይለኛል። ባለታሪኩንም ባናግረው “ካክሱም በፊት ያለውንኳ ብንተወው ተነግሮ ስለማይጨረስ ካክሱም መመሥረት አንሥቶ እስከጣሊያን ወረራ ድረሥ የኢትዮጵያን ታሪክ ብንመረምረው ባለፈው ሃምሣ ዓመት ብቻ * ከውጭ ወራሪ ጋር መተላለቅ፣ ርሥበርሥ መተራረድ ነው ባለም የሌለው አቻ የደም መፍሠሥ ታሪክ ነው ታሪክዋ የኢትዮጵያ ታዲያ መቸ ሠላም አግኝታ ትሻሻል? ይለኛል የታሪኩ ባለሞያ። መንሥኤው ሰው-ሠራሽ ይሁን የእግዜር ቊጣ፣ ወይም የተፈጥሮ ሐቊ ተርበሻል፣ ተራቊተሻል፣ ደምተሻል ኢትዮጵያዬ ምክንያት ቢደረደር አይበጅም ዘንድሮ። እኔ ልጅሽ ግን አምናለሁ፣ ይኸ ቀውጢ ቀንሽ ተሽሮ በጥጋብ፣ በብልጽግና፣ በፍቅር፣ በሠላም ተቀይሮ ዛሬ ለርሀብና ለጦርነት ተጋልጠሽ እንደተዋረድሽ፣ ነገ አንቺነትሽ ተከብሮ አንቺ ለመላው ...