ነጠላ አጀንዳ ለቤተ ክርስቲያን ምስክርነት እንቅፋት ነው
ነጠላ አጀንዳ ለቤተ ክርስቲያን ምስክርነት እንቅፋት ነው ትልቁ ጥያቄ፦ የኢትዮጵያ ወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት ከሚሲዮናዊ ድርጅቶች የገንዘብ እና የማቴሪያል እርዳታ ነፃ የምንወጣው መቸ ነው ? የሚለው ነው። ገንዘብ ወይም " ሥልጠና " ለመቀበል የማንጓዘው መንገድ የለም ! የአሜሪካ ወንጌላዉያንን አካሄድ እንዳ ለ መኮረጅ አቁመን በራሳችን መወሰን የምንጀምረው መቸ ነው ? እነርሱ እድሜ ልክ ተጧሪዎች ተረጂዎች እና ጨቅላዎች ብንሆን ቅር የሚላቸው አይመስልም። በኢትዮጵያ ሕፃናት፣ ሴቶችና ተረጂዎች ስም ገንዘብ ማሰባሰብን አትራፊ ንግድ ያደረጉትን፣ በስማችን እንዳይነግዱ የምናግደው እንዴትና መቸ ነው ? 10 ሺህ ሰው አመነ ተጠመቀ ወይም በሦስት ዓመት 50 ሺህ ፓስተሮች ሥልጠና ተሰጥቷቸው በዲፕሎማ ተመረቁ ( ፎቶ ) ። ( እየቀለድኩ አይደለም ) ፤ 10 ሺህ ቤተ ክርስቲያኖች ተተከሉ ( ፎቶ ) ፣ የሌለ። ማመን ጨርሶ የሚቸግር ! በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ድርጅቶች በዚህ ተግባር ተሠማርተዋል። በአፍሪካ አገራት ካንዱ ወዳንዱ እየዘለሉ። እርግጥ አንዳንድ ቅኖች አይታጡም። ባብዛኛው ግን ራሳቸውን የሚያበለጽጉ ናቸው። ለቤተ ሰቦቻቸው በሕልም ካልሆነ የማይገኝ የገቢ ምንጭ ሥራ ፈጥረዋል። ማርስ ሂል የተሰኘ ከ 10 ዓመት በፊት በህንድ እና በኢትዮጵያ ስም 10 ሚሊዮን ዶላር አርዳታ አሰባስቦ 10 ፐርሰንት ያህል ብቻ ለሁለቱ አገራት አውሏል። የተቀረው እዚሁ አሜሪካ ቀርቷል ! ፍራንክሊን ግራሃም፣ ልጁን ኤድ ግራሃምን አስከትሎ ...