ቤታችን ፈርሶ አላወቅንም












ድንኳናችንን ሌባ ይዞብን ሄደ እኮ!

ሁለት ጓደኛሞች ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ ውለው ጭው ካለ በረሃ ላይ መሸባቸው። ድንኳናቸውን ተከሉና እራት ቀማምሰው ጋደም እንዳሉ እንቅልፍ ይዟቸው ጭልጥ አለ። 
ሌሊት ላይ አንደኛው ከእንቅልፉ ነቃ። ነቃና ሌላኛውን ቀሰቀሰው፣
የተቀሰቀሰው “ምነው ቀሰቀስከኝ?” አለው።
“ቀጥ ብለህ ሰማዩን እይ ልልህ ነው”
የተከናነበውን ገለጠና:- 
“አየሁት … እና?...”
“እና ምን ይታይሃል? ምን ታስተውላለህ?”
“ምን ዓይነት ጥያቄ ነው? ከዋክብት ነዋ!”
“ታዲያ ምን አስተዋልክ?”

ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም ብሎ አሰበና፣ “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደማቅ ከዋክብት አያለሁ፣ … የከዋክብቱ አሠላለፍ በዚህ በግራ በኩል የማንቸስተር ሲቲ አሠላለፍ ይመስላል፤ የባሎቴሊ ጠጉር ቁርጥ ይታየኛል፤ … ጊዜው ዘጠኝ ሰዓት እንደ ሆነ እገምታለሁ፤ … በመንፈሳዊ ዐይን እንየው ካልክ ደግሞ፣ እግዚአብሔር በኃይሉ ታላቅ አምላክ እንደሆነ፣ ሰው ግን ትቢያ እንደሆነ እገነዘባለሁ ...” 
ጓደኛውም ተቀብሎ፣
“አይ ወንድሜ ... ተኝተን ድንኳናችንን ሌባ ይዞብን ሄደ እኮ!...” አለው።

Comments

Popular posts from this blog

HaileSelassie's Band of Armenian Orphans

Blue Revolution

Dust In The Wind

ወሬ

የዐቢይ ወይስ የዓለም ጦርነት