Posts

ተኪኒ ዶሮ እንደ ጣዖስ

  ተኪኒ ዶሮ እንደ ጣዖስ ተኪኒ ዶሮ፦ ወይ ዶሮ አልሆንኩ ወይ ጆፌ አሞራ፤ ይህን እርድ የመሰለ አንገቴን እንደ ተዋበች ስካርፍ ልሠርበት ወይስ ምን ላድርገው ? አለ። ከዘመድ አዝማድ የለየኝ ሰንካላ ዕድሌ ! አለ። አንድ ቀን ከሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በስተ ጀርባ ከግራር ዛፍ ሥር ቊጭ ብሎ ይህንኑ ሲያሰላስል፣ አንድ ራእይ አየ። በራእዩ ውስጥ ያየው ፍጡር እርሱኑ ይመስላል፤ ግን ደግሞ እርሱን አይመስልም። ዐይኔ ነው ? ምንድነው ? አለ። እንደ ጧት ጮራ በመንግሥተ ሰማይ ፀዳል አሸብርቆ ከቊጥቋጦ ጀርባ ብቅ አለ። አጃቢ እንዳስከተለ ሙሽራ በሺህ ዐይኖች ተከብቧል። ገና ሲያየው የተኪኒ ልቡ ትርክክ አለ። እንዳይሸሽ እግሮቹ በመገረም ተሳሰሩ፤ ድረሱልኝ ብሎ እንዳይጣራ ድምጾቹ ጒሮሮው ውስጥ ተሠነጠሩ። ፍጡሩ እየቀረበ መጣ። አከላቱ፣ ባይኑ ፊት ተስፋፍቶ የኅብረ ቀለማት መጋረጃ መሰለ፤ ቀረበ። ቆም አለ። ቆም ብሎ፣ ጣዖስ እባላለሁ ! ስላንተ ወሬ ሰምቻለሁ አለ። ተኪኒ ዶሮ ነፍስ አልቀረለትም፤ ከዚያን ቀን ጀምሮ ጣዖስ ለመሆን ብርቱ ምኞት አደረበት። ማልዶ ወንዝ ዳር ቆሞ የገዛ ፊቱን እያየ፤ የጣዖስን አካሄድና ቅላጼ መለማመድ ጀመረ። አንድ ቀን ከወንዝ ዳርቻ ሲመለስ፣ በራእይ ያየውን ጌጣጌጥ ሜዳ ላይ ተበትነው አገኛቸው። ሚካኤል የልቤን ጸሎት ሰምቶ ዘረገፈልኝ አለ። ልክ እንዳየው አስተካክሎ ከበስተ ኋላው ጌጦቹን ጎንጉኖ አሠራቸው። ወደ ሠፈር ተመልሶ መጣ። ያዩ ሁሉ ምን ጒድ ነው ! አሉ። ...

ቋንቋን በቋንቋ

Image
ቋንቋን በቋንቋ ~ ቋንቋህ ያስጠላል፤ ቋንቋዬ ይበልጣል ~ ስለ ቋንቋ የተለያዩ እይታዎች መኖራቸው አዲስ አይደለም። የሚገርመው ይልቅ፣ ብዙዎች እንደ ሹምና አቡን ትእዛዝ ሲሰጣጡ ማየት ነው። ትእዛዙን ማን፣ እንዴት ይፈጽም ? እይታዎችን ማቀራረብና መተግበርስ ይቻላል ? መቸ በምን ቅደም ተከተል ? ወዘተ። ይህን ያሰቡበት ቢኖሩ ድምጻቸው አልተሰማም። የራስን አጉልቶ፣ የሌላኛውን ማድበስበስ የተለመደ በመሆኑ፣ የጽሑፌ ይዘት ለያንዳንዱ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ የተዘነጉ ጥቃቅን አሳቦችን ማነጋገር ይሆናል። ቋንቋ ቢያንስ ሀ / ድንበር ተሻጋሪ መሆን ይኖርበታል፤ አማርኛ ተናጋሪ፣ እርስ በርሱ ብቻ ከሆነ፣ ከኬላው ውጭ በምን ይግባባል ? ለ / ድንበር ተሻግረን እንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ወዘተ፣ የቆነጠርን ቢያንስ አኗኗራችንን ለማሻሻል እንደ ሆነ አንርሳ ሐ / ቋንቋ ተሻጋሪ እንዲሆን፣ ድልድይ የሚሆን ቋንቋ ይሻል። አማርኛ ድልድይ ነው። እርግጥ፣ ሁሉን ቋንቋ ማወቅ የተሻለ ነበር። ይህ ስላልተቻለ፣ ከቋንቋዎች መርጦ መጠቀም ግድ ሆነ። በአመራረጡ ላይ፣ የፖለቲካ ኃይላት ተጽዕኖ አላሳደሩም ማለት ግን አይደለም። [ ቅኝ ] ገዥዎች፣ ሥርዓተ ትምህርት፣ ሥርዓተ ኃይማኖት፣ የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ ጦርነት፣ ወዘተ፤ ኃይላቱ ተጽዕኖ እያሳደሩ፣ ራሳቸውም የሚለወጡ ናቸው። በህዝቦች ታሪክና ባህል ውስጥ እንደ ነበረ የሚቀጥል የለም። ሰዎች፣ ተደራጊም አድራጊም ነን። ገዢ መደብ ከህዝብና ከአገር ቀድሞ በአንድ ጀንበር አይወለድም። ነገሮች የየራሳቸው ሂደት አላቸው። አንዱ ...