Posts
መንግሥት ተለዋውጦ ሕዝብ የተረሣበት
- Get link
- X
- Other Apps
አገራችን ዓይነተኛ መሪዎች የነበሯት ዘመን ነበር። አገር ወዳድ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ። ምን ያደርጋል ታዲያ? ትውልድ ይጠይቅ ለነበረው ጥያቄ ቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻሉም! ዘገዩ። ከ13 ዓመት በፊት እነ ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ ሞክረው ከከሸፈባቸው የመንግሥት ግልበጣ ምንም አልተማሩም። ከ13 ዓመት በኋላ የባሰ መጣባቸው፤ መንግሥቱ ኃይለማርያም የተባለ ሻለቃ። ሲያዋርዳቸው። እስከ ዛሬ የሚያቃጥለኝ፣ አለህግ አለርኅራኄ መገደላቸው ነው። ከዘውዱ አገዛዝ በኋላ በደርግ ዘመን የተነሡትም የማያሳፍሩ አገር ወዳድ መሪዎች ነበሩ። የቀድሞዎቹ ዘገዩ፤ ያሁኖቹ ተጣደፉ። በጥድፊያ ብዙ አጠፉ። እግዚአብሔርን ናቁ። ያለርኅራኄ ያለፍትኅ ተገዳደሉ። ዛሬ ያለንበት ውድቀት (ከአዲሳባ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛና ከ3ኛ ድግሪ ምሩቃን ብዙዎቹን በንጉሡም በደርግም ከነበሩት ጋር ማስተያየት ጨርሶ የማይታሰብ ነው። ነገሩ ጠ/ሚ ዐቢይ እንደሚሰብኩን አይደለም። አገርን በባዶ ወረቀት/ያለእውቀት፣ በማዕረግና በወዳደቀ ዩኒቨርሲቲ ማልማት ጨርሶ አይቻልም። ሚንስትሩና አብረዋቸው ያሉት ጧት ማታ እንደ ድግምት ብልጽግና ብልጽግና ይሉናል። አገር ለመምራት የበቁ ዜጎችን ማሠልጠን እስካልተቻለ ግን፣ አገራችን የቱሪስት ገንዘብ ማራገፊያ፣ የቱጃር ዐረቦች መናኻሪያ እንኳ ብትሆን፣ ዜጋ ከጫማ ጠራጊነት ከለማኝነት አይወጣም። እህቶቻችን ባልባሌ ሥፍራ ከመዋል ውጭ ለራሳቸውም ላገራቸውም አይበጁም። በገዛ አገር ባእድ መሆን ነው። እነ መንግሥቱ የአፄ ኃይለሥላሴን ስህተት ለማረም ተነሡ። የባሰ አበላሽተው ተወገዱ። እነ መለስ ዜናዊ የአፄ ኃይለሥላሴንም የደርግንም ለማቃናት ተነሡ። የባሰ አንጋድደው፣ ራሳቸውም ተወገዱ። ከእነ መለስ አብራክ የተገኙት ዐቢይ፣ ከ10 ዓመት ንግሥ በኋላ...
World History
- Get link
- X
- Other Apps
Obama Factor: Ethiopians and Their Place in World History by Mitiku Adisu Important paleontological findings of the past three decades have identified Ethiopia as providing the firmest clue to human origins and to ‘conceptual thinking.’ This statement is, however, too general for our present purposes. With Barack Obama taking center stage and Abraham Lincoln’s 200th birthday approaching we may want to revisit specific contributions Ethiopians have made to world community. In an earlier post we cited that the Luo in Kenya, Southern Sudan and possibly Uganda claim Obama as one of their own; Ethiopians, on the other hand, opted to rename him Brook [blessed v. blessing] in the hope that he will be the one blessing we need to end the deception and misery being carried out in the name of democracy. But unlike Kenyans and Sudanese we already have Abe Lincoln, Alexander Pushkin, and Peter Ustinov in our list of notables. How so? Well, Abe Linco...
ምክክር ምክክር ምክር የማይሰማ ማ ይሆን?
- Get link
- X
- Other Apps
የምክክር ኮሚሽኑ የተጠቃለሉ አጀንዳዎችን በሚቀጥለው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ ተገለጸ። የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ2018 ዓ.ም ዋና ዋና ክንውኖችና ቀጣይ ሥራዎችን አስመልክቶ ጷጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ፣ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርአያ (ፕሮፌሰር) የተጠቃለሉ የአጀንዳ የውሳኔ ሐሳቦች መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ ተናገሩ። ይህም የሚሆነው ለተሳናባቾቹ የፓርላማ አባላት ስንብት ከመደረጉ በፊት መሆኑን ተናግረዋል። 400 አጀንዳዎች እየተደራጁ መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፣ መንግሥት የአጀንዳ ትግበራን የሚከታተልበትን የዕቅድ ስትራቴጂ አስመልክቶ ራሱን የቻለ ምክረ ሐሳብ ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆናቸውን አስረድተዋል። [ሪፖርተር ጋዜጣ በፌስቡክ ገጹ፣ መስከረም 1/2019 ዓም] ኮሚሽኑ ምን ያህል ነፃ እንደ ሆነ ይታያል። የገዥው ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ከሆነም ይታያል። የራሱን ሥራ ሪፖርት መንግሥት ሳንሡር ሳያደርገው በቀጥታ ለሕዝብ ማሠራጨት ይችላል? ያ ካልሆነ ኮሚሽነሩ፣ ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ ሥልጣኔን እለቃለሁ ብለው እንደ ነበር አንርሳ! በሌላ ሥፍራ እንዳመለከትኩት፣ የኢትዮጵያ ችግሯ እርስበርስ አለመተማመን ነው፤ መተማመንን ሳይሆን አለመተማመንን ሥራዬ ብሎ የሚዘራ አመራር መኖሩ ነው!